Ethiopian Movement for Unity and Justice ALEJE Member

Home  »  Ethiopian Movement for Unity and Justice

የኢትዮጵያ  የአንድነትና የፍትህ  ንቅናቄ

(ኢአፍን)

የኢትዮጵያ አንድነትና የፍትህ  ንቅናቄ (ኢአፍን) በሀገራችን ላይ የተጋረጠውን የመከፋፈል አደጋና ኢትዮጵያውያን የተነፈጉትን ነጻነት፣ ፍትህና እኩልነት ለማረጋገጥ የሚካሄደውን ትግል ለማስተባበርና ለመደገፍ የተቋቋመ የፖለቲካ ንቅናቄ ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ አንድነቱን በአስተማማኝ ለማረጋገጥ፣ እንዲሁም እኩልነትንና ዲሞክራሲን ለማስፈን የሚችለው በነጻና ርእታዊ ምርጫ የሚፈልገውን መንግስት በማቋቋም ብቸኛ የስልጣን ምንጭነቱን ዕውን ሲያደርግ ብቻ ነው::

ስለሆነም ንቅናቄው በኢትዮጵያ ላይ ያንዣበበውን የመበታተን አደጋ፣ ፍትህ፣ የነጻነት ዕጦት በማስወገድ አገራችን ወደ ተረጋጋና ዘላቂ ዲሞክረሲያዊ ሥርዓት እንድትሸጋገር ሁለገብ ትግል ማድረግ ቀዳሚ አላማው ነው።


1.    ራእይ

ብሔራው አንድነቷና ሉዓላዊነቷ የተጠበቀ፣ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትህ የሰፈንባት፣የግለሰብና የወል መብቶችና ነጻነቶች የተከበሩባት፣ አትዮጵያዊያን ሁሉ በእኩልነትና በኩራት የሚኖሩባት  ታላቂቷ አትዮጵያን እውን ሆና ማየት ነው።

2.   ተልእኮ

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአንድነቱ፣ ለፍትህና፣ ለእኩልነቱ የሚያደርጋቸው ዘርፈ-ብዙ ትግሎች የተደራጁና የተቀንባብሩ እንዲሆኑ የሚቻለውን ሁሉ አስተዋጻኦና ድጋፍ ማድረግ።

3.   መሠረታዊ ዓላማዎች

3.1 የኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ አንድነቱን ጠብቆና ህብረቱን አጠናክሮ በአገሩ ላይ የተንሰራፋውን የውያኔ/ኢህአዴግ ዘረኛና አምባገነናዊ አገዛዝ ለማስወገድ የሚያካሄድውን ትግል ማገዝ፤

3.2. በኢትዮጵያ ውስጥ የብሔራዊ ዕርቅ ዓላማዎችን ተግባራዊ በማድረግ በአገሪቱ ዲሞክራሲያዊ የሽግግር ሥርዓት እንዲፈጠር አስፈላጊ ቅድመ-ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤

3.3. ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች የሚሳተፉበት ሁለአቀፍ የሽግግር መንግስት ተቋቁሞ በነጻና ርእቱዓዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ መንግስታዊ ሥርዓት እስኪመሰረት የአገሪቱን አንድነት: የህዝቡን ሠላምና ደህንነት መጠበቅ፤

3.4. በህዝቡ መካከል የኢትዮጵያዊነትና ወንድማማችነት  ስሜት እንዲጠናከር፣  በፖለቲካ ኅይሎች መካከል  የዕርቅ፣ የመቻቻልና ተባብሮ ለጋራ ሀገርና እድገት የመሥራት ፍላጎትና  ዕምነት እንዲዳብር ማድረግ፤

3.5. አዲሲቱ ኢትዮጵያ ለምስራቅ አፍሪካ አካባቢ የሠላምና የዘላቂ ልማት ዋስትና እንድትሆን ማንኛውንም አይነት ሽብርተኝነት፣አክራሪነትና፣ጽንፈኝነትን መታገል ፤ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲያድግና እንዲጎለብት ማድረግ።


4. የንቅናቄው የትግል ስትራቴጂ

ንቅናቄው ዓላማዎቹን ተግባራዊ ለማድረግ የሀገር ውስጥ፣ የአካባቢአዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በጥልቀት በመመርመር በፖለቲካ፣ በወታደራዊ፣ በዲፕሎማሲ እንዲሁም በቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ዘርፎች ከትግሉ ሂደትና ከወቅቱ ሁኔታዎች ጋር የተገናዘቡ ስትራቴጂዎችና ሥልቶችን እየቀየሰ  ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርግል።

 

Ethiopian Unity and Justice Movement (EUJM)

 

The Ethiopian Unity and Justice Movement (EUJM) is a political entity organized to coordinate and support the struggle of the Ethiopian people against national disintegration, injustice , inequality, and domination and oppression by an ethnic minority regime.

EUJM firmly believes that national unity, sovereignty and equality of all ethnic groups, the political and civic liberties of citizens, and brotherhood among Ethiopians, democracy, economic and social justice are the basic preconditions for stability, sustainable peace and development in the country.

1.   Vision

To ensure that Ethiopia’s national unity and sovereignity are protected; the rule of law  reigns supreme; social and economic justice prevail, and  all Ethiopians live with dignity, equality, basic rights and liberty.

2.  Mission

To support and contribute its share in struggle of the Ethiopian people for unity, justice, equality, and freedom from the reigning ethnocentric dictatorship of the TPLF/ERPDF.

 

3.  Fundamental Objectives

3.1. To support the Ethiopian people to further strengthen national unity and the spirit of cooperation in their struggle for their fundamental rights and freedom; and against the current unjust ethnocentric and oppressive political order.

3.2. To persistently work for the smooth and peaceful transition of state power in the country on the basis of tolerance, mutual understanding, and national reconciliation among all stakeholders.

3.3. To ensure that all power emanates from the people and that a democratic political order is established through free and fair election.

3.4. To work in a determined way to foster the spirit of brotherhood, understanding, cooperation and unity among Ethiopians and all stakeholders, political and otherwise, so that Ethiopian multi-ethnic identity is further strengthened on the basis of equality, justice and freedom for all citizens.

3.5.  To struggle against all sorts of terrorism, extremism and fundamentalism so that Ethiopia becomes the beacon of peace, stability, good governance, and sustainable development in the region.

 

4.  Strategy/Method of struggle

To effectively realize its objectives, EUJM, shall develop, implement, and evaluate specific plans of action and strategies on the basis of a comprehensive analysis of the prevailing domestic, regional and international conditions.

 

ContactEUJM@gmail.com